giziew.org

ድምጿ ተሰማ ቀራንዮ

ከኤድን እስከ ቀራንዮ
Share on facebook
Share
Share on twitter
Tweet
Share on telegram
Telegram
Share on whatsapp
WhatsApp
Share on email
Email
Share on print
Print

ባለማወቅ ሳይሆን በድፍረት

ፈጽመው ትልቅ ኀጢአት

አዳምና ሔዋን ሲወጡ ከዚያ ቤት

ከመልካሙ ኤድን ገነት፤

ከበዛበት መዘዙ

ወደ’ንግዳ ዓለም ሲጓዙ

እየፈሩና እየቸሩ

ከቀድሞ ቤታቸው ሲባረሩ፤

በደልን ተሸክመው

ኃፍረትንም ለብሰው

ደስታን ተሰናብተው

የሕይወትን ዛፍ ትተው፤

እንዳይቀርቡ ወደሱ ጋ

የገነት በር ከኋላቸው ተዘጋ።

ከወጡ በኋላ ከዚያ ሥፍራ

ሔዋን አዝና ስትል ወዮ

ድምጿ ተሰማ ቀራንዮ።

(ተዛማጅ ትርጉም፤ ግርማ ዳምጤ ሀብተየስ፤ ቁርስ፤ ገጽ 160)


የቅርብ ጽሁፎች

በ Facebook ይከተሉን

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *