የብሉይ ኪዳን ትንቢት | የአዲስ ኪዳን ፍጻሜ |
በሠላሳ ብር ተሸጠ |
“የሚበጅ መስሎ ከታያችሁ ዋጋ ዬን ክፈሉኝ፤ … ስለዚህ ሠላሳ ብር ከፈሉኝ። ዘካ. 11፡12 | የአስቆሮቱ ይሁዳ … ምን ትሰጡኛላችሁ?” አላቸው። … ሠላሳ ጥሬ ብር ቈጥረው ሰጡት። ማቴ. 26፡15 |
ክርስቶስ የፋሲካው በግ |
ሙሴ … እንዲህ አላቸው፤ “… ለየቤተ ሰቦቻችሁ የሚሆን ጠቦት መርጣችሁ የፋሲካን በግ እረዱ”። ዘጸ. 12፡21 | ፋሲካችን ክርስቶስ ታርዶአልና፤ 1ቆሮ. 5፡7 |
ከበጉ ምንም አጥንት አይሰበርም |
“የፋሲካ በዓል አከባበር ሥርዐት እንዲህ ነው … (ከበጉ) ምንም አጥንት እንዳትሰብሩ።”ዘጸ. 12፡43-46 | ከወታደሮቹ አንዱ የኢየሱስን ጐን በጦር ወጋው፤ ደምና ውሃ ፈሰሰ። … በመጽሐፍ፣ “ከአጥንቱ አንድም አይሰበርም” ያለው (ተፈጸመ)፤ ዮሐ. 19፡31-36 |
ይተዋል |
አምላኬ፣ አምላኬ ለምን ተውኸኝ? መዝ.22፡1 | ኢየሱስም “አምላኬ፤ አምላኬ፤ ለምን ተውኸኝ?” ብሎ ጮኸ። ማቴ 27፡46 |
ይሳለቁበታል |
የሚያዩኝ ሁሉ ይሣለቁብኛል፤… “በእግዚአብሔር ተማምኖአል፤ እንግዲህ እርሱ ያድነው፤ ደስ የተሰኘበትን፣ እስቲ ይታደገው።” መዝ.22፡7 | የካህናት አለቆችም … እያሾፉበት እንዲህ ይሉ ነበር፤ … በእግዚአብሔር ታምኖአል፤ ‘የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ’ ይል ስለ ነበር እስቲ ከወደደው አሁን ያድነው!” ማቴ 27፡42-43 |
ይጠማል |
ጒልበቴ እንደ ገል ደረቀ፤ ምላሴ ከላንቃዬ ጋር ተጣበቀ፤ መዝ 22፡15 | ኢየሱስም … የመጽሐፍ ቃል እንዲፈጸም፣ “ተጠማሁ” አለ። ዮሐ.19፡28 |
በልብሱ ዕጣ ይጣጣሉ |
ልብሶቼን ተከፋፈሉ፤ በእጀ ጠባቤም ላይ ዕጣ ተጣጣሉ። መዝ. 22፡18 | ወታደሮቹ … ልብሱን ወስደው … ለአራት ተከፋፈሉት፤ እጀ ጠባቡም “ዕጣ ተጣጥለን ለሚደርሰው ይድረስ” አሉ ዮሐ. 19፡23-24 |
ሲሞት መጨረሻ የተናገረው |
መንፈሴን በእጅህ ዐደራ እሰጣለሁ፤ መዝ. 31፡5 | በታላቅ ድምፅ “አባት ሆይ፤ መንፈሴን በእጅህ እሰጣለሁ” ሉቃ.26፡46 |
ሊገድሉት አሤሩ |
የብዙ ሰዎችን ሹክሹክታ እሰማለሁና፤ ዙሪያው ሁሉ ሽብር አለ፤ በእኔ ላይ ባሤሩ ጊዜ፣ ሕይወቴን ለማጥፋት ዶለቱ። መዝ.31፡13 | ጠዋት በማለዳ ላይ፣ የካህናት አለቆችና የሕዝብ ሽማግሌዎች ሁሉ ኢየሱስ ስለሚገደልበት ሁኔታ ተመካከሩ፤ ማቴ 27፡1 |
የቅርብ ወዳጁ ከዳው |
እንጀራዬን ተካፍሎኝ የበላ፣ የምተማመንበትም የቅርብ ወዳጄ፣ በእኔ ላይ ተረከዙን አነሣ። መዝ. 41፡9 | “… ‘እንጀራዬን አብሮኝ የቈረሰ ተረከዙን አነሣብኝ’ የሚለው የመጽሐፍ ቃል እንዲፈጸም ነው። ዮሐ.13፡18 |
ይነሳል |
በመቃብር ውስጥ አትተወኝምና፤ ቅዱስህም መበስበስን እንዲያይ አታደርግም። መዝ. 16፡10 | 9 ስለ ክርስቶስ ትንሣኤ አስቀድሞ አይቶ፥ ነፍሱ በሲኦል እንዳልቀረች ሥጋውም መበስበስን እንዳላየ ተናገረ። ሐዋ.2፡31 |