giziew.org

ይህ ማን ነው?

“አማኑኤል”፤ “ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ”
Share on facebook
Share
Share on twitter
Tweet
Share on telegram
Telegram
Share on whatsapp
WhatsApp
Share on email
Email
Share on print
Print

“ወደ ኢየሩሳሌምም በገባ ጊዜ መላው ከተማ፦ ይህ ማን ነው? ብሎ ተናወጠ”፤ ሉቃስ 19፡37 እና ማቴዎስ 21፡10፤

አዳም ቢጠየቅ፤ የእባቡን ጭንቅላት የሚቀጠቅጠው የሴቲቱ ዘር ነው ብሎ ይመልሳል፤ ዘፍጥረት 3፡15

አብርሃም ደግሞ “የሳሌም ንጉሥ መልከ ጼዴቅ የልዑል እግዚአብሔር ካህን” ይላል፤ ዘፍጥረት 14፡18

ያዕቆብ፤ ገዥነት የተገባው ነገደ ይሁዳ ነው ይለዋል፤ ዘፍጥረት 49፡10

ኢሳይያስ፤ “አማኑኤል”፤ “ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ” በማለት ይመልሳል፤ ኢሳይያስ 7፡14፤ 9፡6

ኤርምያስ፤ የዳዊት ቤት ጻድቅ ቅርንጫፍ፤ “እግዚአብሔር ጽድቃችን” ነው ይላል፤ ኤርምያስ 23፡6

ዳንኤል፤ መሢሕ ነው በማለት ይመልሳል፤ ዳንኤል 9፡25

ሆሴዕ፤ “ሁሉን የሚገዛ አምላክ እግዚአብሔር፣ የሚታወቅበት ስሙም እግዚአብሔር ነው”ይላል፤ ሆሴዕ 12፡5

መጥምቁ ዮሐንስ፤ “የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ” በማለት ስሙን ያውጃል፤ ዮሐንስ 1፡29

ኃያሉ አምላክ እግዚአብሔር፤ “እርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ” በማለት ከዙፋኑ ያውጅለታል፤ ማቴዎስ 3፡17

እኛ ተከታዮቹ ደግሞ፤ ይህ መሲሑ ኢየሱስ ነው፤ የሕይወት ጌታ፤ የዓለም መድኅን በማለት እንመሰክራለን፤

የጨለማው ኃይላት፤ “የናዝሬቱ ኢየሱስ ሆይ፥ … ማን እንደ ሆንህ አውቀናል፥ የእግዚአብሔር ቅዱስ” ነህ በማለት ዕውቅና ይሰጡታል (ማርቆስ 1፡24)።  

(የዘመናት ምኞት፤ ገጽ 579)


Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *