በስሜ የተጠራው ሕዝቤ
ምወደው ከልቤ
አቅንቶ ቢያይ ወደላይ
ቢጠይቅ ከሰማይ
ቢፈልግ የኔን ፊት
ከክፉ ቢመለስ ከርኩሰት
ራሱን አዋርዶ ቢጸልይ
እሰማዋለሁ እኔ አምላክ
እባርከዋለሁ ያለ ልክ፡፡
ከዳር እስከ ዳር
ትፈወሳለች ምድር
የኃጢአትም ይቅርታ
ሳይቆጥብ ሳያመነታ
ያጎናጽፈዋል የኛ ጌታ
ከልብ የፈለቀ ጸሎት
ተመንጥቆ የወጣ ከአንጀት
ያለምንም ጥርጥር
ይመለሳል በተወሰነው ሰዓት
ፈቃዱ ከሆነ መለኮት።
2ዜና 7፡14 (ግርማ ዳምጤ፤ ተማሪው ግርማ፤ ገጽ 17)