መሲሐዊ ሁነት | የብሉይ ኪዳን ትንቢት | የአዲስ ኪዳን ፍጻሜ |
በቤተልሔም ይወለዳል | ሚኪያስ 5፡2 | ማቴዎስ 2፡1 |
ከድንግል ይወለዳል | ኢሣይያስ 7፡14 | ሉቃስ 1፡26-31 |
ከዳዊት ዘር ሐረግ | ኤርምያስ 23፡5 | ራዕይ 22፡16 |
በልጅነቱ የመገደል ሙከራ ይደረግበታል | ኤር. 31፡15፣16 | ማቴዎስ 2፡13-18 |
ወዳጁ ይከዳዋል | መዝሙር 41፡9 | ማቴዎስ 26፡25፣34 |
በ30 ብር ይሸጣል | ዘካርያስ 11፡12፣13 | ማቴዎስ 26፡15 |
በመስቀል ይሰቀላል | መዝሙር 22 እና ዘካርያስ 12፡10 | ማርቆስ 15፡15 |
ልብሱን ዕጣ ይጣጣሉበታል | መዝሙር 22፡18 | ማቴዎስ 27፡35 |
አጥንቱ አይሰበርም | ዘጸአት 12፡46 | ዮሐንስ 19፡31-33 |
በሃብታም መቃብር ይቀበራል | ኢሳይያስ 53፡9 | ማቴዎስ 27፡57-60 |
የሚሞትበት ዓመት፣ ቀን እና ሰዓት | ዳንኤል 9፡ 26፣27 ዘጸአት 12 | ማቴዎስ 27 |
ከሦስት ቀን በኋላ ከሙታን ይነሳል | ሆሴዕ 6፡2 | የሐዋ. ሥራ 10፡40 |
አስደናቂ እውነታ፤ ከላይ ከተጠቀሱት 12 ትንቢቶች ስምንቱ በአንድ ሰው በአጋጣሚ የመፈጸም ዕድላቸው ምን ያህል እንደሆነ በካሊፎርኒያ ግዛት የፓሳዴና ኮሌጅ የሒሳብ፣ የሥነፈለክና የምንድሕስና ትምህርት ክፍል የቀድሞ ኃላፊ የሆኑት ዶ/ር ፒተር ስቶነር ሲናገሩ ከ12ቱ ትንቢቶች 8ቱ ብቻ በአንድ ሰው በአጋጣሚ የመፈጸም ዕድላቸው አንድ ለ 1,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000 ነው ብለዋል። ይህም የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢት አፈጻጸምን አስደናቂ ከማድረግ ባለፈ መጽሐፍ ቅዱስን ተዓማኒ የሚያደርግ ነው።