giziew.org

“ጊዜው መቼ እንደሚሆን አታውቁምና ተጠንቀቁ”

Share on facebook
Share
Share on twitter
Tweet
Share on telegram
Telegram
Share on whatsapp
WhatsApp
Share on email
Email
Share on print
Print

የጌታችንና የመድኃኒታችን ክርስቶስ የምድር አገልግሎት ወደመጠናቀቂያው ሲቃረብ ደቀመዛሙርት ወደ እርሱ ቀርበው ስለ ዳግም ምፅዓቱና ስለ ፍጻሜ ዓለም ጠይቀውት ነበር። መድኃኒዓለምም ሁኔታውን በዝርዝር ካስረዳቸው በኋላ የምፅዓቱን ቀንና ሰዓት ማንም እንደማያውቅ በመንገር ይህንን እንዲያደርጉ አሳሰባቸው፤ “ስለዚህ ጊዜው መቼ እንደሚሆን አታውቁምና ተጠንቀቁ፤ ትጉ፣ ጸልዩም” (ማርቆስ 13፡33)።

ይህንን የጌታ ቃል መሠረት በማድረግ እና የዘመኑን ፍጻሜ በመረዳት የመጽሔታችንን ስም “ጊዜው” በማለት ሰይመን እነሆ አሁን ለንባብ መብቃት ችላለች። ለዚህ ሁሉ ስብሃት ለአብ፤ ስብሃት ለወልድ፤ ስብሃት ለመንፈስ ቅዱስ ይሁን! አሜን!

ጊዜው መጽሔት ላሁኑ በየሁለት ወሩ እየታተመች በአገር ውስጥና በውጪ የምትሰራጭ ሲሆን በውስጧ ስምንት መደበኛ ዓምዶችን ያካተተች ነች። እነዚህም፤

የጥሞና መልዕክት፤ አጠር ያለ፤ አንባቢያን በጸጥታና በርጋታ ሊያሰላስሉበት የሚገባ ተከታታይነት ያለው መልዕክት የሚቀርብበት፤

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፤ አንድን የመጽሐፍ ቅዱስ ርዕስ ወይም ክፍል ለጥናት በመውሰድ በተከታታይ ጥልቅ ትንታኔ የሚሰጥበት፤

ለጤናችን፤ “ሰውነታችን የእግዚአብሔር ቤተመቅደስ” የመሆኑ ምስጢርና ከዚያ ጋር በተያያዘ አኗኗራችንና ጤና አጠባበቃችን ከአምልኳችን ጋር እየተመጋገበ የሚሄድ መሆኑ የሚዳሰስበት፤

“አንባቢው ያስተውል”፤ ጌታ ክርስቶስ ዳግም የመምጣቱን ሁኔታ ሲያስረዳ ምልክቶቹን በምናይበት ጊዜ “አንባቢው ያስተውል” እንዳለው፤ “ጊዜው” መድረሱን የሚያመለክቱ፤ የትንቢት ፍጻሜዎችንና የዘመኑን ሁኔታ የሚያገናዝቡ የዜና ዘገባዎች የሚቀርቡበት፤

ቤተሰብ፤ በኤድን ገነት በእግዚአብሔር የተመሠረቱት ሁለት ተቋማት ሰንበትና ቤተሰብ ከመሆናቸው አኳያ የቤተሰብ አመሠራረትና አመራር ከመንፈሣዊ ህይወታችን ጋር ያለው ቁርኝት የሚዳሰስበትና ትንታኔ የሚሰጥበት፤

ይህ ነው ታሪኬ፤ ሰዎች እንዴት ክርስቶስን ወደማወቅ ህይወት እንደመጡ፣ ህይወታቸው እንዴት እንደተለወጠ፣ እግዚአብሔርን ለመከተልና በመንገዱ ለመጓዝ ውሳኔ ሲያደርጉ ከጠላት የመጣባቸው ጥቃት ምን እንደነበርና እንዴት እንደተቋቋሙት እንዲሁም እስካሁን በእምነት የመቆየታቸውን ምሥጢር ምን እንደሆነ የሚቀርብበት፤

የመዳን ታሪክ፤ በሰማይ የተጀመረው ታላቁ ውዝግብ እንዴት ወደ ምድር እንደደረሰና የሰውን ልጅ ምን ዓይነት ሁኔታ ውስጥ እንዳስገባው፤ እንዲሁም ይህ ውዝግብ በምን መልኩ እንደሚጠናቀቅ በተከታታይ የሚተነተንበት፤

ጥያቄና መልስ፤ ከእናንተ የተወደዳችሁ የዝግጅታችን ተሳታፊዎች የሚደርሱንን ማንኛውንም መንፈሣዊ ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ሙከራ የምናደርግበት ዓምድ ነው። ያሏችሁን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎች ላኩልን፤ እናስተናግዳለን።

ስለዚህ ጊዜው መጽሔትን በዚህ መልኩ በማቀናበር ለእናንተ ለንባብ አድርሰናልና ሁሉን አዲስ ማድረግ የሚችለው አምላካችን በዚህ አዲስ ዓመት ይህችን አዲስ መጽሔት ለህይወታችን መታደሻ ያድርግልን።

“ስለዚህ ጊዜው መቼ እንደሚሆን አታውቁምና ተጠንቀቁትጉጸልዩም

መልካም ንባብ።

ጊዜው መጽሔት!


Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *