giziew.org

ሊቀጳጳስ ፍራንሲስ የመጀመሪያውን የአረብ ምድር ጉዞ ያደርጋሉ

“የሰላምህ ማስተላለፊያ አድርገኝ” በሚል መሪ ርዕስ የሚደረገው ይህ ጉዞ መልካም አስተሳሰብ ያላቸው ሰዎች ለሰላም እንዴት ተባብረው መሥራት እንደሚችሉ ማሳያ ነው።
Share on facebook
Share
Share on twitter
Tweet
Share on telegram
Telegram
Share on whatsapp
WhatsApp
Share on email
Email
Share on print
Print

የሮም ካቶሊክ ቤ/ክ ርዕሳነ ሊቀጳጳሳት ፍራንሲስ በጥር ወር መገባደጃ አካባቢ በቤ/ክኗ ታሪክ የመጀመሪያ የሚባለውን ጉብኝት በተባበሩት የአረብ ኤምሬትስ በአቡዳቢ ከተማ እንደሚያደርጉ ቫቲካንን ጠቅሶ ሬውተርስ ዘግቧል። ሕዝብ የሚጋበዝበት ሥርዓተ ቅዳሤ በአቡዳቢ እንደሚያደርጉም ተነግሯል።

ይህ ከጥር 26 – 28፤ 2011 ዓም የሚደረገው የፍራንሲስ ጉብኝት በሃይማኖቶች መካከል ሊኖር ስለሚገባው ሰላም ትኩረት እንደሚሰጥ ተነግሯል። ሊቀጳጳስ ፍራንሲስ ጉብኝት እንዲያደርጉ ጥሪው የመጣው ከአቡዳቢው አልጋወራሽ ሼክ ሞሐመድ ቢን ዘይድ አልናህያንና በዚያ ከሚገኘው በጣም ጥቂት ከሆነው የካቶሊክ ማኅበረሰብ እንደሆነ ከቫቲካን የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ሊቀጳጳስ ፍራንሲስና ታላቁ ኢማም ሼክ አሕመድ ኤል-ጣይብ

እስልምና የመንግሥት ሃይማኖት በሆነበት የባህረ ሠላጤው አካባቢ ክርስትናን በይፋ የመከተል ነጻነት እንደየአገራቱ ይለያያል። በአረብ ኤምሬትስ እና በኩዌት ክርስቲያኖች የተለየ ፈቃድ በማውጣት በቤተክርስቲያናት ማምለክ ይችላሉ። የእስልምና ቅዱሳት ሥፍራዎች በሚገኝባት ሳዑዲ አረቢያ ግን ማንኛውም ሃይማኖት የተከለከለ ነው።

“የሰላምህ ማስተላለፊያ አድርገኝ” በሚል መሪ ርዕስ የሚደረገው ይህ ጉዞ መልካም አስተሳሰብ ያላቸው ሰዎች ለሰላም እንዴት ተባብረው መሥራት እንደሚችሉ ማሳያ ነው በማለት የቫቲካኑ አፈቀላጤ ተናግረዋል። ይህ ርዕስ የተወሰደው በ12ኛው ክፍለዘመን መጠናቀቂያ አካባቢ የነበረው የአሲሱ ፍራንሲስ ከተባለው መነኩሴ የሰላም ጸሎት መጽሐፍ ነው።

ጉብኝቱን አስመልክቶ አልጋወራሹ በትዊተር ገጻቸው እንደተናገሩት፤ ሊቀጳጳሱ “የሰላም፣ የመቻቻልና የወንድማማች መዋደድ ምልክት ናቸው፤ ጉብኝቱ በሕዝቦች መካከል በሰላም አብሮ መኖር አስመልክቶ የመወያያ ዕድልን ይከፍታል ብለን በተስፋ እንጠብቃለን” ብለዋል።

የአዘጋጆቹ ማስታወሻ፤ በሃይማኖቶች መካከል ግንኙነትና ሰላም መፍጠር መልካም ሆኖ ሳለ የሃይማኖት ድርጅቶች ከመንግሥታት ጋር በመተባበር የሚፈጥሩት ግንኙነት በሃይማኖትና በመንግሥት መካከል ጋብቻን ወደ መመሥረት የሚያደርስ ይሆናል። በመካከለኛው ዘመን እንደታየው መንግሥት ከሃይማኖት ጋር ሲቀላቀል ሁሉንም ሊወክል የማይችለው ቤተእምነት በመንግሥት ድጋፍ የራሱን ሃይማኖት ይፋዊ እንዲሆን በማድረግ ይህንን አንቀበልም በሚሉ ላይ ስደትንና መከራን ሲፈጽም ቆይቷል። ይህ ዓይነቱ ተግባር በመጨረሻው ዘመን እንደሚገም መጽሐፍ ቅዱስ በራዕይ 13 ላይ ይናገራል። ዓለምም ይህንን ዓይነቱን የአብያተእምነቶች ውኅደትን ሲያይ እንደሚደነቅ በራዕይ 13፡3 ላይ እናነባለን።

“አንባቢው ያስተውል”


Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *