giziew.org

ግንቦት 6፤ 2012! ዓለምአቀፍ ውል የሚፈረምበት ቀን

ምድራችንን ለመታደግና የአካባቢን ብክለት ለመቀነስ ከሳምንቱ አንድ ቀን እሁድ እንደ ሰንበት ሊታረፍበት የሚገባ ቀን መሆኑን ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ አመልክተዋል
Share on facebook
Share
Share on twitter
Tweet
Share on telegram
Telegram
Share on whatsapp
WhatsApp
Share on email
Email
Share on print
Print

የሮማ ካቶሊካዊት ቤ/ክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በመጪው ግንቦት ወር ዓለምአቀፍ ውል የሚፈረምበት ቀን እንዲሆን ጥሪ አደረጉ። ወጣቶችን ባዲስ መልኩ ማስተማር እንደሚገባ ተናገሩ።

ምድራችንና ሰብዓዊው ዘር ለገጠመው ከፍተኛ ተግዳሮቶች የዓለማችን የፖለቲካና የሃይማኖት መሪዎች፣ ታዋቂ ሰዎች፣ ምሁራን፣ ዓለምአቀፋዊ ድርጅቶች፣ የምጣኔሃብት ምሁራን፣ ሳይንቲስቶች፣ ፖሊሲ አውጪዎች፣ የኪነጥበብ ሰዎች፣ ታዋቂ ስፖርተኞችና ወጣቶች ግንቦት 6፤ 2012ዓም (ሜይ 14፣2020ዓም) ወደ ቫቲካን በመምጣት ዓለምአቀፋዊ ትብብር ለመመሥረት ውል በመግባት ለሰው ልጅ የሚበጅ የወደፊት ተስፋ መመሥረት የሚቻልበትን ስምምነት መፈረም አለባቸው ብለዋል ፖፕ ፍራንሲስ።  

ተሰብሳቢዎቹ “የጋራ ቤታችን” ስለሆነችው ምድር በመወያየት በሥነትምህርት ላይ ዓለምአቀፍ ተግባቦት በመፍጠር የወደፊቱን ትውልድ ይህችን ምድር እንዴት መንከባከብ እንዳለበት የሚማርበት ስልት እንደሚቀይስ የቫቲካን መግለጫ አመልክቷል። የዓለም ሕዝብ በፍጥነት እየጨመረ የምድር መበከል አሳሳቢ ደረጃ ላይ በመድረሱ አካባቢያችንን በመንከባከብ ምድርን መታደግ የሚቻልበት ስልት እንዲቀየስ የፖፕ ፍራንሲስ ሃሳብ ነው። “የተሻለች ዓለም ለመፍጠር” ታዳጊውን ትውልድ ማስተማርና ወጣቶች ላይ ተጽዕኖ ማሳደር በቀዳሚነት ሊሠራበት እንደሚገባ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ተናግረዋል።

ፖፕ ፍራንሲስ ለስብሰባው እንዲረዳ እኤአ ግንቦት 24፤2015ዓም በላቲን ቋንቋ Laudato si በአማርኛው “ውዳሴ ለአንተ ይሁን” በሚል ርዕስ ያወጡትን ባለ 184 ገጽ ሐዋርያዊ መልዕክት (ኢንሳይክሊካል) ለግብዓትነት አቅርበዋል። በዚህ ጽሁፍ ላይ ምድራችንን ለመታደግና የአካባቢን ብክለት ለመቀነስ ከሳምንቱ አንድ ቀን እሁድ እንደ ሰንበት ሊታረፍበት የሚገባ ቀን መሆኑን አመልክተዋል። ለአካባቢ ጥበቃ እሁድ ቀን ይታረፍ ነው የሚሉት ፖፕ ፍራንሲስ።

የአዘጋጆቹ ማስታወሻ፤ መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ እንደሚናገረው ፍጥረት በተጠናቀቀ ጊዜ እግዚአብሔር ባርኮና ቀድሶ የሰጠው ቀን ቀዳሚት ሰንበትን እንደሆነ ይናገራል (ዘፍጥረት 1 እና 2)። ይህም የሰንበት ቀን የተሰጠው “አይሁድ” የሚባለው ሕዝብ ከመጀመሩ እጅግ በርካታ ዓመታት በፊት መሆኑን ልብ ይሏል። ጌታችንና መድኃኒታችን ክርስቶስም በምድር በነበረ ጊዜ ልምምዱ በቀዳሚት ሰንበት ቀን ወደ ምኩራብ መሄድ እንደነበር መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል (ሉቃ. 4፡16)። ይህንን የሰንበት ቀን ወደ እሁድ ከመቀየር ባለፈ በዓለም በሙሉ የአምልኮ ቀን እንዲሆን በመጨረሻው ዘመን በዓለማችን ታላቅ በድንቅና በተዓምራት የታጀበ ሥራ እንደሚሠራ ራዕይ 13 ያስረዳል።         

“አንባቢው ያስተውል”


የቅርብ ጽሁፎች

በ Facebook ይከተሉን

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *